ዋሽንግተን ዲሲ —
የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ 19 ስርጭት እና አዝማሚያን ለመረዳት ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ግብዓት እና ቴክኖሎጂካዊ ብልሃቶች እንደሚያስፈልጉ ባለሙያዎች ይመሰክራሉ።
ኢትዮጵያ ይሄንን ቫይረስ ለመግታት የምታደርገውን ጊዜ የማይሰጥ ርብርብ ለማገዝ ያቀዱ በጎ ፈቃደኞች ፤ «ኢትዮጵያ-ኮቪድ 19 ማህበረሰብ» የተሰኘ የበይነ- መረብ ላይ የፈጠራ እና ምርምር ትብብር መስርተዋል።
በተለይ በዮናይትድ ስቴትስ እና አውሮጳ የሚኖሩ ከ300 በላይ ትውልደ-ኢትዮጵያዊያንን በ3 ቀናት ውስጥ ለማስተባበር እንደቻለ የተነገረለት ማህበረሰብ የጤናው ዘርፍ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ፣የመረጃ አሰባሰብ ፣ስርጭት እና ትንበያ ብልሃቶችን ለመገንባት እየጣረ ስለመሆኑ ከአስተባባሪዎቹ አንዱ ሚካኤል እንዳለ ይናገራል።
ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ።