በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናትድ ስቴትስ በኮቪድ የሞቱት ሰዎች ከ900ሺ አለፈ


.
.

በዩናይትድ ስቴትስ በኮቪ6 19 የሞቱት ሰዎች ቁጥር ትናንት ዓርብ ከ900ሺ ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መረጃውን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ይህ ቁጥር “የተወዳጅ እናቶች አባቶች የልጅ ልጆች ህጻናት ወንድሞች እህቶች ጎረቤቶችና ወዳጆች ሁሉ ነው” ብለዋል፡፡​

“አሁን ከመቸውም ጊዜ በላይ መከላከያዎቹ ሁሉ አሉን፣” ያሉት ባይደን አሜሪካውያን በሙሉ እንዲከተቡ አሳስበዋል፡፡

የጆን ሀፕኪንስ የኮረና ቫይረስ መረጃ ማዕክል፣ ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ በመላው ዓለም የኮቪድ ተጋላጮች ቁጥር 391 ሚሊዮን መድረሱንና የሟቾችም ቁጥር ወደ 6 ሚሊዮን መቃረቡን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG