በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በለይቶ ማቆያ ስፍራዎች ለሚገኙ የመጽሃፍት ልገሳ ተደረገ


ብሔራዊ ቤተ-መጽሃፍት እና ቤተ-መዘክር ኤጀንሲ
ብሔራዊ ቤተ-መጽሃፍት እና ቤተ-መዘክር ኤጀንሲ

በሺዎች የሚቆጠሩ አንባቢያን የሚያዘወትሯቸው ቤተ-መጽሃፍት የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት በተቀመጡ የጥንቃቄ ትዕዛዞች ምክንያት ለጊዜው ተዘግተዋል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ-መጽሃፍት እና ቤተ-መዘክር ኤጀንሲ በዚህ ሰዓትም ቢሆን መጽሃፍት እና አንባቢያን እንዳይነጣጠሉ በማሰብ አዳዲስ ስራዎችን መጀመሩን አስታውቋል።

ከሰሞኑ ከፀሐይ አሳታሚ ድርጅት ጋር «እናንብብ ፣እናብብ » የተሰኘ ሀገራዊ የንባብ መርሐ-ግብር በመጀመር ታዋቂ ሰዎች በመገናኛ ብዙሐን ላይ በመቅረብ የንባብ አፍታዎች እንዲያቀርቡ አድርጓል።

ከሰሞኑ ደግሞ በለይቶ ማቆያዎች ውስጥ ለሚገኙ ከ1ሺ በላይ ግለሰቦች የመጽሃፍ ልገሳ ማድረጉን ኤጀንሲው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግሯል።

የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ይኩኑ አምላክ መዝገቡ ልገሳው በለይቶ ማቆያዎች ውስጥ የሚገኙ በአንድ በኩል የንባብ ባህላቸውን እንዲያሻሽሉ በሌላ በኩል ደግሞ ሁኔታው ከሚፈጥረው አሉታዊ ድባብ ራሳቸውን ለመታደግ እንደሚጠቅማቸው ተስፋ አድርገዋል።

ከአቶ ይኩኑ አምላክ መዝገቡ ጋር የተደረገው አጭር ቆይታ ያዳምጡ ።

ለለይቶ ማቆያ ስፍራዎች የመጽሃፍት ልገሳ ተደረገ።
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:20 0:00


XS
SM
MD
LG