ማራኪ ተስፋዬ የ"ጀግኒት ኢትዮጵያ" መስራች ናት፡፡ የ"ጀግኒት" እንቅስቃሴ በማህበራዊ ሚዲያው የተጀመረው ለላቁ ሴቶች እውቅና ለመስጠት፣ የሴቶችን ጥቃት ለመቃወም እና በሴቶች ዙሪያ ያሉ ተቋማትን እንዲተሳሰሩ ለማድረግ ነው፡፡
ማራኪ ተስፋዬ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ወደ ሃገር ካለቀረጥ እንዲገባ ከወዳጆቿ ጋር በመሆን ብዙ ጥራለች፡፡ ወጣት ሴት ተማሪዎች እና አካል ጉዳተኞች ጽዱ እና ምቹ የሆነ የመጸዳጃ ቤት አገልግሎት እንዲያገኙ 1000 የሚሆኑ መጸዳጃ ቤቶችን በትምህርት ቤቶች ውስጥ ከመገንባት ውጥን አድርጋ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡ በሕይወቷ የምታሳካቸውን ነገሮች በሙሉ በመርህ እንደምታደርግ ትገልጻለች፡፡ አሰበች፤ አቀደች፤ አሳካች ይህ እሷ ወጣቶች እንዲከተሉት የምትመክረው መርህ ነው፡፡