በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለየኔታ ቤት ፦ ምጥን ቆይታ ከዮሃንስ ዘርፉ ጋር


.
.

መኖሪያውን በቤልጂየም ሀገር ያደረገው የሶስት ልጆች አባት ዮሐንስ ዘርፉን ፣ ያሳስቡት ከነበሩ ጉዳዮች አንዱ ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ስለ ሀገራቸው ባህል እና ታሪክ እንዲያውቁ የሚያደርግ የተደራጀ መርሀ-ግብር አለመኖሩ ነበር።ይሄ ምክንያት የኃላ ኃላ «የኔታ ቤት» የተሰኘውን የቴሌቭዥን መርሐ-ግብር ለመጀመር መነሻ እንደሆነው ይናገራል።

«የየኔታ ቤት» ዘወትር ቅዳሜ እና እሁድ በኢትዮጵያ ልጆች የቴሌቭዥን ጣቢያ ይታያል። አቀራረቡ አዝናኝ ፣ግቡ ደግሞ ማስተማር ነው።በህጻናት ዘንድ የተወደደለትን «ዮዮ» የተሰኘ ገጸ-ባህሪ በመጠቀም መርሐ-ግብሩ ሀገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮችን ህጻናት በሚረዷቸው መንገዶች ያቀርባል። የቀን ተቀን ጥያቄዎቻቸውን የሚመልሱ አዝናኝ ማብራሪያዎችንም ያሰናዳል።ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰሩ የህጻናት ፊልሞችን ወደ አማርኛ መልሶ ያሳያል።

ከ2009 ዓመተ-ምህረት ጀምሮ ይሄንን አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው «የየኔታ ቤት» በዋናነት የሚንቀሳቀሰው በግል በሚደረግ የጉልበት እና የገንዘብ ፈሰስ እንደሆነ ዮሃንስ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግሯል።

ለህጻናት በሚሆኑ ስራዎች ውስጥ ተጠምደው የነበሩት የመርሐ-ግብሩ አዘጋጆች ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎችን ለመደገፍ በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎችን ለማሰባሰብ ተንቀሳቅሰዋል።ከ70ሺ በላይ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎችን ቤልጂየም ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለማስረከብ ዝግጅት በሚደረግበት ዋዜማ ሀብታሙ ስዩም ስለ«የኔታ ቤት!» የበለጠ ለማወቅ የመርሐ-ግብሩን መስራች ዮሃንስ ዘርፉን በስልክ አግኝቷል።

ምጥን ቆይታቸውን ያዳምጡ፦

ስለ የኔታ ቤት፦ምጥን ቆይታ ከዮሃንስ ዘርፉ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:50 0:00


XS
SM
MD
LG