ዋሽንግተን ዲሲ —
አዲስ አበባ ጎጃም በረንዳ አካባቢን የሚያዘወትር ሰው ወጣቱን በጎ አድራጊ ዘካሪያስ ኪሮስን ያወቀዋል። ዘካሪያስ እጅ አጥሯቸው ጎዳና የወደቁትን ይመግባል፣ ለአረጋዊያን የንጽህና አገልግሎት ይሰጣል፥ የዘመመ ጎጃቸውን ይጠግናል። እሱ እና አጋሮቹ የሚያደርጓቸውን መልካም ግብሮች በማህበራዊ መገናኛዎች የሚያዩ ኢትዮጵያን የተቻለቸውን ይደግፋሉ። የተገኘውን ይዞ ዘካሪያስ ርዳታ ወደ ሚያስፈልጋቸው ወገኖች ቤት ይመላለሳል።
"አንዳንድ ጊዜ ሰጭ የነበሩ ሰዎች ተቀባይ፣ የሚያጎርሱ የነበሩ እራሳቸው ጎራሽ ሆነው ታገኛቸዋለህ"ሲል የኮቪድ 19 ወረርሽኝን መቀስቀስ ተከትሎ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የሚናገረው ዘካሪያስ ፣ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ከማህበራዊ መገናኛ ተከታዮቹ ጋር በመሆን ለማገዝ ጥረቱን መቀጠሉን ይናገራል።
ሀብታሙ ስዩም ከወጣቱ መልካም አድራጊ ዘካሪያስ ኪሮስ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።በመቀጠል ይደመጣል።