በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልጅነታቸውን በግጭቶች የተቀሙ የኢትዮጵያ ህጻናት ጉዳይ


ልጅነታቸውን በግጭቶች የተቀሙ የኢትዮጵያ ህጻናት ጉዳይ
ልጅነታቸውን በግጭቶች የተቀሙ የኢትዮጵያ ህጻናት ጉዳይ

ዓለም አቀፉ የግዛት ውስጥ መፈናቀል ተቆጣጣሪ ማዕከል በምኅጻሩ IDMC ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት እስከ አውሮጳዊያኑ ታህሳስ 31 /2018 ባለው ጊዜ በተደረገ ቆጠራ ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች በግጭቶች ምክንያት ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ ይፋ አድርጓል፡፡

ግጭት እና መፈናቀሉ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በክፉ የዳሰሰ ቢሆንም ፣በይበልጥ ጫናውን ያሳረፈባቸው በህጻናት እና ሴቶች ላይ ስለመሆኑ የረድኤት ድርጅቶች በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት (ዪኒሴፍ) ፣ ባለፈው የአውሮጳዊያን ዓመት ጥቅምት ላይ ይፋ ባደረገው ሪፖርት 1.5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ከቀያቸው የመፈናቀል ክፉ ዕጣ እንደገጠማቸው ይፋ አድርጓል፡፡

ይህ ክስተት በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለው ስነልቦናዊ እና አካላዊ ጉዳት በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት ለመላው ሀገር የሚተርፍ ጦስ እንደሚመዝ በህጻናት ላይ የሚሰሩ የረድኤት ድርጅቶች እያሳሰቡ ነው፡፡ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ ሴቭ ዘ ቺልድረን ( ህጻናትን አድን) የተሰኘው ተቋም ነው፡፡

ከተቋሙ ባለሙያዎች ጋር ቆይታ ያደረገው የአሜሪካ ድምጹ ሀብታሙ ስዩም ፣ግጭቶች በኢትዮጵያዊያን ህጻናት ላይ እየፈጠሩ ስላለው ዘርፈ- ብዙ ፈተና ጠይቋል፡፡

ልጅነታቸውን በግጭቶች የተቀሙ የኢትዮጵያ ህጻናት ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG