በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለይቶ ማቆያ ስፍራዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ የምህንድስና መስፍርቶች ምንድን ናቸው?


የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተለያዩ ሀገራት ህዝቦች ላይ የፈጠረውን ውጥንቅጥ ቀድሞ በመመልከት መሰል ሰብዓዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጥፋት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይፈጠር ለማድረግ በሙያቸው ለማገልገል ከተሰማሩት የሙያ ማህበራት አንዱ የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ነው።

ከተመሰረተ 30 ዓመታት ያለፈው ማህበር ሀገሪቱ የኮቪድ 19 ህመምተኞችን ለመለየት እና ለማከም የምትጠቀምባቸውን ስፍራዎች የምህንድስና መስፈርት የሚመለከት ምክረ- ሀሳብ ለጤና ሚኒስቴር እና ለከተማ እና ልማት ሚኒስቴር አንዳቀረበ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል።

የሚሊየኒየም አዳራሽ ወደ ህክምና መስጫ ስፍራ በተቀየረ ማግስት ጀምሮ ማህበሩ ባደረጃው የኮቪድ 19 የበጎ ፈቃደኞች ቡድን እየታገዘ ሙያዊ ድጋፍ ማድረጉን የሚናገሩት የማህበሩ ፕሬዚደንት አቶ አማኑኤል ተሾመ ፣ በቀጣይ ጊዜያት የገበያ ቦታዎችን ጨምሮ ህዝብ የሚበዛባችው ስፍራዎች ለጤና ምቹ የሚሆን አወቃቀር እንዲኖራቸው የሚያግዝ ሙያዊ መመሪያ ለማሰናዳት ዕቅድ መኖሩንም አውስተዋል።

አቶ አማኑኤል ተሾመን ያናገራቸው ሀብታሙ ስዩም ሲሆን የቃለ -ምልልሱ ቅጂ ከስር ይገኛል።

ለይቶ ማቆያዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ የምህንድስና መስፈርቶች ምንድን ናቸው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:23 0:00


XS
SM
MD
LG