በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህጻናትን ዳግም ከተፈጥሮ ጋር ያቀራረበው "ኑ ጭቃ እናቡካ!"


.
.

አፈር መፍጨት ፣ጭቃ ማቡካት ውሃ መራጨት ። ብዙዎቻችን ያለፍንበት የህጻንነት ዘመን ትውስታ ነው። አሁን አሁን የስልክ እና የኮምፒተር ጨዋታዎች የብዙ ህጻናትን ትኩረት ከመሳባቸው በፊት የሚያዘወትሯቸው “ልብ አርስ “ ጨዋታዎችም ነበሩ።

አሁን ላይ አንድ ተቋም ይሄን ቀደምት የጨዋታ አውድ በዘመናዊ ሁኔታ በማደረጀት ወላጆች እና ህጻናት ከተፈጥሮ ጋር ዳግም እንዲቀራረቡ እየጣረ ይገኛል

“ኑ ጭቃ እናቡካ!” የተሰኘው ተቋም፣ በስሙ የተሰየሙ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ህጻናት እና ወላጆች የተሳተፉባቸው የአደባባይ ትርኢቶች (ፌስቲቫሎች) አዘጋጅቷል። ከዚህ በተጨማሪ ህጻናት ሀገር በቀል የዕደ ጥበብ ክህሎቶችን እንዲለምዱ ስልጠናዎችንም ሲሰጥ ሰንብቷል።

የዚህ ሀሳብ ጠንሳሾች ባልና ሚስቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ - ሀመረ-ሙሉጌታ እና ዮሴፍ ወልደ አማኑኤል ናቸው።

በዚህ ዝግጅት ለየት ስላለው ጅምራቸው እና ተያያዥ ጉዳዮች ያጫውቱናል። ያነጋገራቸው ሀብታሙ ስዩም ነው።

ህጻናትን ከተፈጥሮ ጋር ዳግም ያቀራረበው “ ኑ ጭቃ እናቡካ !”
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:28 0:00


XS
SM
MD
LG