በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያው የ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ዘመዶቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች፣ አሜሪካ ቦይንግን ለፍርድ እንድታቀርብ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን በተከሰከሰበት ሥፍራ የነፍስ አድን ሰራተኞች እየሰሩ ነው።
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን በተከሰከሰበት ሥፍራ የነፍስ አድን ሰራተኞች እየሰሩ ነው።

በዋሽንግተን የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናት፣ እ.አ.አ በ2019 ዓ.ም የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰከሰበት ወቅት ዘመዶቻቸውን ካጡ ቤተሰቦች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ቤተሰቦቹ፣ የፍትህ ሚኒስትር በቦይንግ ኩባንያ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሰርት ጠይቀዋል።

እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም ቦይንግ በ737 ማክስ አውሮፕላኖቹ ላይ ከተገኘ የአሠራር ጉድለት ጋር በተያያዘ በቀረበበት የማጭበርበር ሴራ ክስ እንዳይመሰረትበት ስምምነት ላይ ደርሶ ነበር።

ቦይንግ ህይወታቸውን ካጡ ተሳፋሪ ቤተሰቦች ጋር በሚስጥር ስምምነቶችን ሲያደርግ ቢቆይም፣ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰው የመከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች ግን ክስ እንዲመሰረት በዩናይትድ ስቴትስ ፍትህ ሚኒስትር ላይ ግፊት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

ረቡዕ እለት በተካሄደው ውይይት፣ የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባለስልጣናት ተቋሙ ጉዳዩን እያጤነው እንደሆነ ለዘመዶቻቸው ገልጸውላቸዋል።

ከስብሰባው በኃላ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የቤተሰብ አባላት በፍትህ ሚኒስትር ላይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። በአደጋው አባቷን ጆሴፍ ኩሪያን ያጣችው ዚፖራ ኩሪያ "ዛሬ ከፍትህ ሚኒስትሩ ጋር የነበረኝ ስብሰባ ተስፋ አስቆርጦኛል" ያለች ሲሆን "ከእንግዲህ የፍትህ ጉዳይ ወይም የእኛ የፍትህ መጓደል ብቻ አይደለም፣ የህዝባዊ ደህንነት ጉዳይም ነው" ስትል ስሜቷን አጋርታለች።

የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቦይንግ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ ከሆነ "ትግሉን እንደሚቀጥሉ" የቤተሰቦቹ ጠበቃ ፖውል ካሴል አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG