ጥቂት ስለ አዲስ አበባ የጎዳና ሰዓሊያን

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ አህጉር ዲፕሎማቲክ መናገሻ የሆነችው አዲስ አበባ ላይ ውበት ለመጨመር የወጠኑ ወጣቶች እንቅስቃሴ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለወትሮው በማስታወቂያ ወረቀቶች ውበታቸውን አጥተው የነበሩ የመንገድ ዳር ግንብ እና ግድግዳዎችን በውብ የስዕል ስራዎች አስጊጠዋል፣ ተስፋቸውን እና ህልማቸውን ለተመልካች አቅርበዋል።