ከጥቂት የኢትዮጵያ ስፍራዎች በስተቀር መላ ሀገሪቱን ዞሮ ለጎበኘው እና ላስጎበኘው ሄኖክ ስዩም የጉዞ ትርጉም ፍካት የተሞላበት ነው።የጉዞን ያክል ሊያስደስተው እና ሊረካው የሚችል ጉዳይ አለመኖሩን ደጋግሞ የሚያነሳው ለዚሁ ይመስላል።
ከህጻንነቱ ጀምሮ ልቡን ያሸፈተው፤ አዳዲስ ነገሮችን የማየት ጉጉት፣ የማሰስ ፣የመጎብኘት ግፊት፤ የኃላ ኃላ የጋዜጠኝነት ህይወትን ከተቀላቀለ በኃላ በርትቶበት የሙሉ ጊዜ ተጓዥ ፣ ጎብኝ እና አስጎብኝ እንዲሆን አሸፍቶታል።
ለኢትዮጵያ ያለውን ፍቅር በአያቱ ስም ስፍራ በመተካት ሄኖክ ስዩም ሀገሬ እየተባለ መጠራት የጀመረው ወጣት ከ10 ዓመታት በላይ የሀገሪቱን ውብ ገጽታዎች ላላዩት ለማሳየት ለፍቷል። ጉዞን የሚመለከቱ የህትመት ውጤቶችን፣ የቴሌቭዥን ትርኢቶችን በማሰናዳትም ብዙሀን እሱ ያየውን በርቀትም ቢሆን እንዲቃመሱ አድርጓል።
ስራው ግን የራሱ ፈተናዎች አሉት።ከዱር አራዊት ጋር መፋጠጥ፣ ጉልበት እና መንፈስ የሚፈትን ጎዳና ማቆራረጥ ፣ አሁን አሁን ደግሞ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ የሚፈጥራቸውን ድንገቴ ሁነቶች ጋር መገጣጠም ሊመጣ ይችላል። እንዲህም ቢሆን ግን የሀገር ጉብኝትን እና የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃን ከተመለከቱ እንቅስቃሴዎች ሄኖክ የሚያፈገፍግ አይመስልም።
ሀብታሙ ስዩም ከ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ጋር ያደረገውን ምጥን ቆይታ ያዳምጡ
Your browser doesn’t support HTML5