የዛሬ አምስት አመታት ገደማ ጽዮን ኪሮስን አንዳች የወላጅነት ሀሳብ ይንጣት ገባ፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ —
ልጇቿ ከመጽሃፍት ጋር ወዳጆች እንዲሆኑ የምትጥረው የሁለት ልጆች እናት፣በወቅቱ ለልጆቿ የምታነባቸው እና ልጆቿን የምታስነብባቸው መጽሃፍት በባዕድ ቋንቋ የተጻፉ ፣የባዕድ ኑሮ የሚተርኩ የመሆናቸው ጉዳይ ከነከናት፡፡
‹‹ልጆቼ ከአድዋ መንገድ ይልቅ ኦክስፎርድ ስትሪትን ያውቁ ነበር›› ስትል የምታስታውሰው ጽዮን ፣ያ ጭንቀት ‹‹ሚዳቆ›› የተሰኘ መላ እንድትፈጥር አደረጋት፡፡
‹‹ሚዳቆ›› በጽዮን እና አጋሮቿ የተመሰረተ የህጻናት መጽሃፍት አሳታሚ ድርጅት ሲሆን፣ ከ10 በላይ የተረት፣ከ50 በላይ ደግሞ የንባብ ማስተማሪያ መጽሃፍትን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለገበያ አቅርቧል፡፡
ሀብታሙ ስዩም በጋቢና መደብር መሰናዶው ከጽዮን ኪሮስ ጋር አውግቷል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5