ዋሽንግተን ዲሲ —
ፊልሞችን፥የኢንተርኔት ላይ ቴሌቭዥኖችን እና የመሳሰሉትን በማሰራጨት ረገድ "ኔትፍሊክስ " እና "አማዞን" የተሰኙት የአሜሪካ ኩባንያዎች ግንባር ቀደም ናቸው።
የእነዚህን ተቋማት አበርክቶት በመከተል ፤ለኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን የሚሆኑ መርሃ -ግብሮችን ለማሰራጨት ያቀደ ድርጅቱ በቅርቡ ስራ ጀምሯል።
የድርጅቱ ስም “ሀበሻ ቪው” ሲሆን፤ኑሯቸውን በውጭ ሀገራት ባደረጉ ሶስት ትውልደ -ኢትዮጵያዊያን የተጀመረ አገልግሎት ነው።
ሀብታሙ ስዩም እንግሊዝ ሀገር ከምትገኘው ፥ከድርጅቱ መስራቾች መካከል አንዷ ከሆነችው(የድርጅቱ የስራ ክንውን ሃላፊም ናት) ፤ትዕግስት ከበደ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።
Your browser doesn’t support HTML5