የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም እውቀት ምን ማለት ነው? ለምንስ ያስፈልጋል?

የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም እውቀት

በኢትዮጵያ የመረጃ አጠቃቀም እውቀት አናሳ መሆኑን ተከትሎ፣ ሆን ተብሎም ሆነ ባለማወቅ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበረሰቡ ላይ ቀጥተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ገልፀዋል። በማህበራዊ ድህረ-ገፆች አማካኝነት የሚተላለፉ አሳሳች መልእክቶችን ጉዳት ለመቀነስም ህብረተሰቡ በመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን እውቀት ማዳበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለመሆኑ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ምን ማለት ነው? በተለይ የማህበረሰብ ሚዲያ ከፍተኛ ተጠቃሚ የሆነው ወጣት እውነተኛ መረጃን ከሀሰተኛ መለየት የሚችለው እንዴት ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ስመኝሽ የቆየ በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ሁለት ምሁራንን ጋብዛ አነጋግራለች። እንግዶቿ በኦሃዮ ክፍለ ግዛት ኬንት ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ ወርቃለማሁ እና በሚኖሶታ ክፍለ ግዛት ሀምሊን ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር እንዳልካቸው ሀይለሚካኤል ጫላ ናቸው።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም እውቀት ምን ማለት ነው? ለምንስ ያስፈልጋል?