ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ ሲኒማ ላይ ስለደቀነው ፈተና |ቆይታ ከፊልም ባለሙያው ሄኖክ አየለ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በርካታ ኪነ-ጥበባዊ እንቅስቃሴዎች እንዲገቱ ምክንያት ሆኗል። ኢትዮጵያ ውስጥ በግለሰቦች ቀዳሚ ጥረት ውስጥ በርካታ ተመልካቾችን በማፍራት ላይ የነበረው የፊልም ዘርፍ ከሰሞኑ አዳዲስ መሰናክሎች ተጋርጠውበታል። የተወሰኑትን እናነሳሳ ዘንድ- ታዋቂውን የፊልም ባለሙያ ሄኖክ አየለን አነጋግረናል። የወንዶች ጉዳይ1፣ዐልቦ እና ፔንዱለምን የመሰሉ ፊልሞችን ያዘጋጀው ሄኖክ ሰሞነኛ ሁነቶችን ያስረዳል።መደረግ ይገባል የሚለውን መላም ያካፍላል።