በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞና ድጋፍ ሰልፎች ተካሄዱ

ትዕይንተ-ህዝብ በዋሺንግተን ዲሲ

ዛሬ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ መንግስትን የሚያወግዙ እና የሚደግፉ ተገኝተው ድምጻቸውን ሲያሰሙ አርፍደዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራውን መንግስት የተቹት ሰልፈኞች ፣አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ቆይታው ፈጽሟቸዋል ያሏቸውን በደሎች ለታዳሚው አጋርተዋል፡፡

በአንጻሩ በሀገር ቤት ያለው አስተዳደር ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ሰላም እና ዲሞክራሲ እንድትሻገር›› እየተጋ ነው ያሉ ሰልፈኞች፣ ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡትን ወቅሰዋል፡፡

ሀብታሙ ስዩም ‹‹ኢንተርናሺናል ድራይቭ›› ከተሰኘው ጎዳና ወዲያ እና ወዲህ ሆነው መፈክር ሲያሰሙ ከነበሩት መካከል ከተወሰኑት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በዮናይትድ ስትቴትስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት-ለፊት ትዕይነተ-ህዝብ ተደረገ