"በዓመት ከ1000 በላይ ለሚሆኑ አካል ጉዳተኞች ሰው ሰራሽ እግር የመስጠት ዕቅድ አለን"

.

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ዜጎች በተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በደረሰባቸው የአካል ጉዳት እንደፍላጎታቸው መራመድ (መንቀሳቀስ) ተስኗቸዋል።እነዚህ ዜጎች ዳግም መራመድ ይችሉ ዘንድ የሚያግዙ ሰው ሰራሽ አካላት በበቂ መጠን አለመገኘታቸው ደግሞ የዜጎች ችግር የበረታ እንዲሆን አድርጓል።

ይሄን የተመለከቱ ነዋሪነታቸውን በእንግሊዝ ለንደን ያደረጉት አቶ ሰለሞን አማረ በበኩላቸው ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን በርካቶች ዳግም የሚራመዱባቸውን-ሰው ሰራሽ እግሮች በማዘጋጀት እያደሉ ይገኛሉ። ሀቅማቸው በተለያዩ ምክንያቶች በመወሰኑ የፍላጎታቸውን ያህል ሰው ሰራሽ አካላትን እያመረቱ ማቅረብ እንደቸገራቸው የሚናገሩት አቶ ሰለሞን፣ ደጋፊዎችን ማግኘት ከቻሉ በዓመት ከ1000 በላይ የሚሆኑ ሰው ሰራሽ አካላትን እያመረቱ ለማቅረብ ዕቅድ እንዳላቸው ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ስለ ሰሞነኛ ስራቸው የበለጠ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም በስልክ መስመር አግኝቷቸዋል።

* ይህ ቃለምልልስ ከተደረገ በኃላ አቶ ሰለሞን አማረ እና አጋሮቻቸው ሰው ሰራሽ አካላትን የሚያመርቱበት ማዕከል በኢትዮጵያው ፕሬዚደንት ዶ/ር አቢይ አህመድ እንደተጎበኘ ተሰምቷል።

Your browser doesn’t support HTML5

"በዓመት 1000 ለሚሆኑ አካል ጉዳተኞች ሰው ሰራሽ እግር የመስጠት ዕቅድ አለን"