በኢትዮጵያ ሴት ተማሪዎች ከወንድ አቻዎቻቸው በበለጠ ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ትምህርት ቤት የሚገቡ ሴት ህፃናት ቁጥር ከግዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢሄድም አሁንም ሴት ተማሪዎች አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች የሚማሩ በመሆናቸው ከወንድ አቻዎቻቸው በበለጠ ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ። ቀድመው ከነበሩት በሴቶች ትምህርት ዙሪያ ግንዛቤ ማነስ፣ የአቅም ውሱንነት፣ ያለእድሜ ጋብቻና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች በተጨማሪም፣ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት የሚስተዋለው ህገወጥ ስደት ለሴት ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ ምክንያት መሆኑን የትምህርት ባለሙያዎች ያስረዳሉ።