በነቀምቴ የመጀመሪያውን የሴቶች የብስክሌት ቡድን ስላቋቋመችው ወጣት በጥቂቱ

Your browser doesn’t support HTML5

በነቀምቴ ከተማ የተወለደችው ወጣት ሙርቲ ዱጋ ሰኚ 13 ብስክሌቶች እና የስፖርት አልባሳት ለከተማው ሴት ተማሪዎች ከሰሞኑ አበርክታለች። ሙርቲ በእንግሊዝ አገር ውስጥ የብስክሌት ውድድሮች ላይ ስትሳተፍ መቆየቷን ጠቁማ "ይሄን በጎ ተግባር ያከናወንኩትም ሴቶች በብስክሌት ስፖርትና ትምህርታቸው ምሳሌ እንዲሆኑ" ነው ስትል ለጋቢና ቪኦኤ ገልጻለች።