ቆይታ ከሰብአዊ ድጋፍ አሰባሳቢው ሙሉ ኃይለስላሴ ጋር

ሙሉ ኃይለስላሴ በመላ ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያንን በማስተባባር ከ3ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሰብአዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ ችሏል።

ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከለጋሾች በማሰባሰብ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ምክንያት ለኢኮኖሚያዊ ችግር ለተዳረጉ ሰዎች እርዳታ እየሰጠ ያለ አንድ ወጣት እናስተዋውቃችሁ::

ሙሉ ኃይለስላሴ ይባላል። በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ነዋሪ ነው:: እስከ አሁን ካሰባሰበው ገንዘብ ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ የሚሆነውን ወጪ በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች የምግብ እርዳታ እንደተደረገ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግሯል።::

የሙሉጌታ አፅብሃን ዘገባ ያዳምጡ ::

Your browser doesn’t support HTML5

ቆይታ ከሰብአዊ ድጋፍ አሰባሳቢው ሙሉ ኃይለስላሴ ጋር