"ስለ እናንብብ እናብብ " ሀገራዊ የንባብ ዘመቻ ፤ቆይታ ከኤልያስ ወንድሙ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ በቢሊየኖች የሚቆጠር ህዝብ ከቤት እንዲውል ምክንያት ውሏል። ኢትዮጵያዊያንም ከዚህ የዓለም አዲስ ልምድ አልተነጠሉም። በርካቶች ከእንቅስቃሴዎች ተቆጥበው፣ አስጨናቂዎቹን ቀናት እየገፉ ይገኛሉ። እንዲህ ያለውን ጊዜ ለመልካም ፍሬ ለማብቃት የወጠኑት የብሄራዊ ቤተ-መጽሃፍት ኤጀንሲ እና ዋና መቀመጫውን በዮናይትድ ስቴትስ ያደረገው ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት ግን ከአንድ ዘመቻ ጋር ብቅ ብለዋል።