ህጻናትን ከተፈጥሮ ጋር ዳግም ያቀራረበው “ ኑ ጭቃ እናቡካ !”

Your browser doesn’t support HTML5

አፈር መፍጨት ፣ጭቃ ማቡካት ፣ ውሃ መራጨት ። ብዙዎቻችን ያለፍንበት የህጻንነት ዘመን ትውስታ ነው። አሁን አሁን የስልክ እና የኮምፒተር ጨዋታዎች የብዙ ህጻናትን ትኩረት ከመሳባቸው በፊት የሚያዘወትሯቸው “ልብ አርስ “ ጨዋታዎችም ነበሩ ። አሁን ላይ አንድ ተቋም ይሄን ቀደምት የጨዋታ አውድ በዘመናዊ ሁኔታ በማደረጀት ወላጆች እና ህጻናት ከተፈጥሮ ጋር ዳግም እንዲቀራረቡ እየጣረ ይገኛል ።