የዞን ዘጠኝ ተከሣሾች የመሃል ዳኛው እንዲቀየሩ ጠየቁ

  • መለስካቸው አምሃ

ዞን ዘጠኝ

የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሐፊዎች

Your browser doesn’t support HTML5

የዞን ዘጠኝ ተከሣሾች የመሃል ዳኛውን ተቃወሙ

እሥር ቤት ውስጥ የሚገኙት ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሐፍት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ከዚህ በኋላ ጉዳያቸውን እንዳይመለከቱ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል፡፡

አቤቱታ ያቀረቡባቸው ዳኛ ግን በራሣቸው ፈቃድ ጉዳዩን ላለማየት መወሰናቸውን ገልፀዋል።

ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ከተከሳሾቹ አንዱ አቤል ዋበላ እሥር ቤት ውስጥ ግፍ እንደተፈፀመበት ለፍርድ ቤቱ አቤት ብሎ መፍትሔ እንዲሰጠው አመልክቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አመሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡