ሁጢዎቹ አቡ ዳቢ ላይ ያደረሱት ጥቃትና ምላሹ
Your browser doesn’t support HTML5
በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የአረብ ሃገሮች ወታደራዊ ጥምረት የሁጢዎች ይዞታ በሆኑ የየመን ዋና ከተማ፣ ሰንዓ አካባቢዎች ላይ ባለፈው ሌሊት “ከባድ” የተባለ የአየር ድብደባ አድርሰዋል።
ጥምረቱ ድብደባውን ያደረሰው ሁጢዎቹ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ ትናንት የድሮንና የሚሳይል ጥቃት ከፈፀሙ በኋላ ነው።
በጥቃቶቹ ሲቪሎችን ጨምሮ የህይወትና የንብረት ውድመት መድረሱ ተገልጿል።