የአፍሪካ ወጣት መሪዎች በዋሺንተን ዲሲ

የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጅማሮ፤ የማንዴላ-ዋሺንግተን ፌሎሺፕ

“እናንተ የነገ ሳይሆን የዛሬ መሪዎች ናችሁ” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጅማሮን የማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎሺፕ የዚህ ዓመት መርኃግብር ስብሰባ ትናንት ዘግተዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ወጣት መሪዎች በዋሺንግተን ዲሲ

“እናንተ የነገ ሳይሆን የዛሬ መሪዎች ናችሁ” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጅማሮን የማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎሺፕ የዚህ ዓመት መርኃግብር ስብሰባ ትናንት ዘግተዋል፡፡

ስብሰባው ከሰኞ እስከ ረቡዕ ለዘለቁት ቀናት ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ተካሂዷል፡፡

የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጅማሮ ወይም በእንግሊዝኛ ስሙ ምኅፃር - ያሊ እየተባለ የሚጠራው መርኃግብር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የዛሬ ሦስት ዓመት ያስጀመሩት የልምድ መለዋወጫና የዩናይትድ ስቴትስ የሕይወትና የአመራር ዘይቤ ማስተዋወቂያ ግንኙነት ነው፡፡

በዚህ መርኃግብር የሚታቀፉ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የአፍሪካ ወጣቶች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እየዘለቁ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት፣ የመንግሥት፣ የሕዝብና የግል መ/ቤቶችና ንግዶች እንደዚሁም መደበኛ ዜጎች መኖሪያ አካባቢዎች እየተገኙ የአሜሪካን ልምድ ይቀስማሉ፡፡

አምስት መቶ ወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች የተሣተፉበት በማንዴላና በዋሺንግተን የተሰየመው ይህ የግንኙነት መርኃግብር ሁለተኛው ዙር ስድስት ሣምንታት ሲካሄድ ቆይቶ የማጠቃለያ ጉባዔውን ከሰኞ ሐምሌ 27 እስከ 29 / 2007 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ ተጠናቅቋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡