እውን አፍሪካውያን ለቻይና የኮሮና ቫይረስ ስጋት ናቸውን?

Your browser doesn’t support HTML5

የኮሮና ቫይረስ መነሻ የሆነችው ቻይና አሁን አሁን ከበሽታው አገግማ ወደ ነፍስ እየዘራች ነው፡፡ አሁን ላይ ቻይና ውስጥ ያለው የቫይረሱ ስጋት ቀንሶ ከወጪ ሃገራት የሚመጡ ዜጎችን መፈራት ተጀምሯል፡፡ ታዲያ አፍሪካውያን በተለየ መልኩ የመገለልና፣ ወደ ገበያ ቦታዎች እንዳይገቡ፣ የሆቴል ሆነ ቤት እንዳይከራዩ እየተከለከሉ ይገኛሉ፡፡ ይህ የመጤዎች ጥላቻ በመባል የሚታወቀው ማግለል ኢትዮጵያውያንም ላይ አጋጥሟል፡፡ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ምላሽ ሰጥተዋል፦