የዓለም ጤናና አረጋዊያን

የዓለም አረጋዊያን ደኅንነትና ምቾች ማሣያ ካርታ /ሰማያዊ በጣም ጥሩ፤ ቀይ በጣም መጥፎ/




አምለሰት ቴዎድሮስ - የኸልፕኤጅ-ኢንተርናሽናል የታንዛኒያ ዳይሬክተር

Your browser doesn’t support HTML5

የዓለም ጤናና አረጋዊያን


ሰኞ፤ መጋቢት 29 የዓለም የጤና ቀን ነው፤ ዕለቱን ምክንያት በማድረግም መንግሥታዊ ያልሆነው ዓለምአቀፍ ድርጅት ኸልፕኤጅ - ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ 76 ሚሊየን አዛውንት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን ተነፍገው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ኸልፕኤጅ “ዕድሜ ተግባር ይጠይቃል” ሲል በሰየመው ዘመቻው ከዕድሜ ጋር የተያያዙ ችግሮችንና የአገልግሎቶች አቅርቦቶች የሚገኙበትን ደረጃ ለማስተዋወቅ እየጣረ ነው፡፡

የኸልፕኤጅ-ኢንተርናሽናል


የኸልፕኤጅ-ኢንተርናሽናል የታንዛኒያ ዳይሬክተር የሆኑት አምለሰት ቴዎድሮስ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ዕድሜ ተግባር ይጠይቃል” የሚለው ዘመቻ ግብ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከመሪዎቻቸው ጋር በቀጥታ መነጋገር እንዲችሉ የተጠናከረ አቅም እንዲኖራቸው ማድረግ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡