በስቶኮልም በተካሔደ የዳያመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቲች ድል ቀንቷቸዋል

Your browser doesn’t support HTML5

ስዊድን ስቶኮልም በተካሄደ የዳያመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛእስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ባጠናቀቁበት በ1500 ሜትር ሴቶች፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ ስታሸንፍ፣ ዲሪቤ ወልተጂና ሂሩት መሸሻ ተከትለዋት ገብተዋል።

በ800 ሜትር ውድድር ደግሞ ወርቅነሽ መሰለ አንደኛ በመሆን አሸንፋለች። በ5000 ሜትር ሴቶች ኬንያዊቷን ቢትሪስ ቺቤትን ተከትለው ኢትዮጵያውያኑ ለምለም ኃይሉና መዲና ኢሳ 2ኛና 3ኛወጥተዋል። ስቶኮልም የሚገኘው ዘጋቢያችን ኢቢሳ ነገሰ አትሌቶቹን አነጋግሯቸዋል።

አስተያየታቸውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።