ልጆቻችን ባህላቸውን ታሪካቸውን እና ቋንቋቸውን በአጠቃላይ የመጡበትን ሲያውቁ በራሳቸው ይኮራሉ።
ዋሽንግተን —
ለዚህም ስል ከልጆቼ ጋር ሆኘ “ሰብሰብ በሉ” የኢትዮጵያውያን የባህል ስብስብን መሰረትኩ።
እኤአ ከ2009 ዓም ጀምሮ በተቋቋመው ስብስብ አማካይነት ወጣቶች በየቦታው እየተዘዋወሩ ባህላዊ እና ታሪካዊ ትርዒቶችን እናሳያለን። ልጆቻችን በማህበረሰቡ አድናቆትን አትርፈዋል ይላሉ መስራችዋ ወይዘሮ ሶስና አሰፋ ።
በሰሞኑ የሰሜን ኣሜሪካ ኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫልም ላይ ስብስባቸው እየተሳተፈ ነው።
ከቡድኑ መስራች ወ/ሮ ሶስና አሰፋ ጋር የተደረገ ቆይታ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5