በደሴ ከተማ እና በተሁለደሬ ወረዳ የመሬት መንሸራተት አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በደሴ ከተማ እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተትና መስረግ አደጋ፣ከ400 በላይ ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ መስፈራቸውን፣ የሁለቱም አካባቢዎች አመራሮች

አስታወቁ።

የደሴ ከተማ የከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ፣ በአደጋው ቤታቸው የፈረሰባቸውንና ለአደጋው ተጋላጭ ይኾናሉ ተብለው የተለዩ ሰዎችን፣ በደረቅ ወይራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሰፍሩ ማድረጉን ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ፣ በተሁለደሬ ወረዳ ቆርኬ በተባለ አካባቢ በተከሠተው የመሬት መንሸራተትና መስረግ አደጋ፣ ከ15ሺካሬ ሜትር በላይ መሬት ጉዳት ሲደርስበት፤ ሰብሎች፣ ቋሚ ተክሎች እና የግጦሽ ቦታ ከጥቅም ውጭ መኾናቸውን፣

የአካባቢው ግብርና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል ።

በአደጋው ከቤታቸው የተፈናቀሉት የደሴ ከተማ ነዋሪዎችም ኾኑ የእርሻ መሬታቸው የተጎዳ አርሶ አደሮች፣ “ለከፋ ችግር ተጋልጠናል፤” ብለዋል፡፡