ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ጥሪ አስተላለፈ

Your browser doesn’t support HTML5

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰው ትምህርት መጀመራቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው አሁንም ከ1500 የሚልቁ ተማሪዎች አለመመለሳቸውን አስታውሶ ለተማሪዎቹ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ ከቤተሰቦቻቸው ለተመለሱት ተማሪዎች የማካካሻ ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅቶላቸው ያለፋቸውን ትምህርት እንዲከታተሉ እየተደረገ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡