ከአሥር ዘጠኙ የዓለማችን ሕዝብ የተበከለ አየር ይተነፍሳል

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የቤት ውስጥ አየር ብክለት ከፍተኛና ዋናው በውል ያልታወቀ ችግር መሆኑን የገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት/WHO/ ከአሥር፣ ዘጠኙ የዓለማችን ሕዝብ የተበከለ አየር እንደሚተነፍስ አስታወቀ። በቅርቡ ይፋ የሆነው የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት በሰጠው መግለጫ፣ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ፣ በአየር ብክለት ሕይወቱ እንደሚያልፍ ገልጧል። በዚህም ዋናዎቹ ሰለባዎች አፍሪካና እስያ መሆናቸው ተመልክቷል።