በዛሬው ዕለት፣ በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ታስቦ የሚውለው የነፃነት ቀን፥ በሙዚቃ፣ በሰልፍ ትዕይንቶች፣ በተለይም፣ ለበዓሉ ልዩ ድምቀት በሚሰጡ ርችቶች ደምቆ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
እአአ ባለፈው 2022፣ በአገሪቱ ዙሪያ ከርችት ሽያጭ የተገኘው ገቢ 2ነጥብ3 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር፣ የርችት ሥራ ባለሞያዎች ብሔራዊ ማኅበር መረጃ ያመለክታል፡፡ ርችት መተኮስ፣ እንዴት የበዓሉ ዋናው አካል ሊኾን ቻለ? መደረግ ያለበት ጥንቃቄስ?
አሶሺዬትድ ፕሬስ ከሚዙሪ ሴንት ሉዊስ ከተማ ስለ በዓሉ ታሪካዊ እና ባህላዊ አመጣጥ ያጠናቀረውን ሰፊ ሪፖርት ይከታተሉ፡፡