በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ኢጃጂ ከተማ በተፈጠረ ግጭት በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ኢጃጂ ከተማ በወጣቶችና ፀጥታ አካላት መካከል በተከሰተው ግጭት አራት ፖሊሶችና ሁለት ወጣቶች መቁሰላቸውን ፖሊስና ከቆሰሉ ወጣቶች ቤተሰብ ገልፀዋል። ፖሊስ ግጭቱ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆነዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ሦስት የወረዳው ኦርቶዶክስ ካህናትና 50 ገደማ ወጣቶችን ማስሩን አስታውቋል። የምዕራብ ሸዋ ሀገረ-ስብከት ስለጉዳዩ እንደሚያውቅ ገልፆ ችግሩን በሰከነ ሁኔታ መያዝና መፍታት ያስፈልጋል ብሏል::