በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሁለት ሰው መገደሉን የወረዳው አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡
ዋሽንግተን —
በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሁለት ሰው መገደሉን የወረዳው አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡
በግጭቱ አንድ ሰው መቁሰሉና ብዙዎች መታሠራቸው ታውቋል፡፡
ቀበሌዎቹ አባ አማንና ወልተሲስ ይባላሉ። አባ አማን ውስጥ አንድ መስጅድ በመንግሥቱ ኃይሎች መቃጠሉን የቪኦኤ የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ከቦታው ያነጋገራቸው ነዋሪ ገልፀዋል።
ሁኔታው የተከሰተው ቅዳሜ፤ ነኅሴ 21 / 2008 ዓ.ም እርምጃው ቦታው የአሸባሪዎች መሰብሰብያ ነው በሚል የተወሰደ መሆኑን ነዋሪው አመክልተው ቦምብ ተወርውሮ ከ20 በላይ ሰው መገደሉን እኚሁ ተናግረዋል።
እርምጃ የተወሰደው “መንግሥትን በኃይል እንዲንዱ በተላኩት የሻዕብያ ተላላኪዎች፣ በኦነግ፣ በግንቦት ሰባት፣ አርበኞች የሚባሉ ናቸው” ሲሉ የመሰላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ አብዱራህማን ለቪኦኤ ገልፀው በአካባቢው “የተቃጠለም ይሁን የፈረሰ መስጅድም ሆነ ቤት የለም” ብለዋል፡፡
ከመቶ በላይ ሰው በቁጥጥር ሥር መዋሉንና ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ አብዱራሕማን ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5