በኦሮምያ የሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎችን ለማነጋገር የሀገር ሽማግሌዎች ወደሥፍራው ተጓዙ

Your browser doesn’t support HTML5

ምዕራብ ኦሮምያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎችን ለማነጋገር የአገር ሽማግሌዎችና ምሁራን ጋር ወደ አካባቢው መሄዳቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ገልፀዋል። ኃላፊው አቶ ጌታቸው ባልቻ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል "ጥያቄ ያለው አካል ካለ እሁንም ለመነጋገርና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በራችን ክፍት ነው" ብለዋል።