እስላማዊ ታጣቂዎች በአፍሪካ የሳህል አካባቢዎች እያደረሱት ያለው ጥቃት እንዳይዘነጋ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

እስላማዊ ታጣቂዎች በአፍሪካ የሳህል አካባቢዎች እያደረሱ ያሉትን ጥቃትና የምዕራብ አፍሪካን የባህር ዳርቻ ወደ ሚያዋስኑት ግዛቶች እያደረጉት ያለው መስፋፋት በመንግሥታት ችላ እንዳይባል ተንታኞች አስጠነቀቁ። አብዛኛው ዓለም ትኩረቱን ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ወረራ ማድረጉ በጉዳዩ ላይ መዘናጋትን እንዳይፈጥርም ጠይቀዋል።

የፈረንሳይ የጸጥታ ኃይሎች ብቃት ያለው ወታደራዊ ምላሽ መስጠት ይችሉ ዘንድ የአካባቢውን የጦር ኃይሎች በማሰልጠን እየረዱ መሆናቸው ተጠቁሟል።