ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው ቅዳሜ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ መሆኑን፣ ከጥቃቱ የተረፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ጥቃቱን በማውገዝ ባወጧቸው መግለጫዎች፣ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በተካሔደ 6 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ዘመቻ ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መከላከያ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጸው መላው ኅብረተሰብም እንዲተባበር ጠይቀዋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/