ሰነዶችን በርቀት መፈረም የሚያስችለው “ውለታ” ሥራ ጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለጉዳዮች፣ በአካል መገኘት ሳይፈልጋቸው በርቀት ሳሉ፣ በሰነዶች ላይ ፊርማቸውን ማኖር የሚችሉበት “ውለታ ቴክኖሎጂ”፣ ካለፈው ሳምንት አንሥቶ ሥራ እንደ ጀመረ አስታወቀ፡፡

የውለታ ቴክኖሎጂ መሥራች እና የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኬብሮን ደጀኔን ድርጅታቸው ቀደም ሲል ቪዲቸር በሚል የውክልና እና የጉዞ ሰነዶችን ከርቀት ሆኖ በማስፈረም፣ ለዳያስጶራው ማኅበረሰብ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

አሁን በግለሰቦች ደረጃ ብቻ ሳይሆን ለድርጅቶችም ጭምር፣ በተለያዩ ቋንቋዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ አቶ ኬብሮን ገልጸዋል።

ድርጅቱ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በአፍሪካ ደረጃም አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን፣ አቶ ኬብሮን አስታውቀዋል፡፡

ቀሪውን ከተያያዘው የድምፋይል ያድምጡ፡፡