የወላይታ ተወላጆች ሰላማዊ ሰልፍ በሶዶ

Your browser doesn’t support HTML5

በክልል የመደራጀት መብትና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በብሄሩ ተወላጆች ላይ በማንነታቸው የሚፈፀም ጥቃት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አርብ ዕለት በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በሰልፉም በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት መንግሥት እንድያስቆም ለሰልፍ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ጠይቀዋል፡፡
ሰርተው ለመለወጥና በአገሪቱ ልማት ውስጥ አሻራቸውን ለማረፍ የወደዱ የወላይታ ልጆች ተንቀሳቅሰው የመስራት መብታቸው መገደቡንም የገልፁት ሰልፈኞቹ በአገሪቱ ታይቷል ከሚሉት ለውጥ እኩል ተጠቃሚ መሆን እንፈልጋለን ነው የሚሉት፡፡
በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የወላይታ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው የዞኑ መንግሥት የህዝቡን አደራ ተቀብሎ በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡