የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ አወዛጋቢው የድንበር ፖሊሲ ሊሰረዝ እንደሚችል ተጠቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኢሚግሬሽንን በሚመለከት ባለፈው ሳምንት የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ በደቡቡ የሀገሪቱ ድንበር በኩል የሚመጡ ፍልሰተኞች አያያዝ ሊቀየር እንደሚችል ይጠበቃል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ውሳኔ የባይደን አስተዳደር በትረምፕ አስተዳደር ዘመን ሥራ ላይ የዋለውንና ፍልሰተኞች ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ ውሳኔ እስከሚሰጣቸው ድንበሩ ላይ በሜክሲኮ በኩል ቆይተው እንዲጠብቁ የሚያስገድደውን ፖሊሲ ለመሰረዝ እያደረገ ያለውን ጥረት ይደግፋል።

ባለፈው ሳምንት ውስጥ ሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ፍልሰተኞችን በድብቅ ሲያጓጉዙበት በነበረው እና ቴክሳስ ሳን አንቶንዮ ከተማ ባቆሙት የጭነት መኪና ውስጥ ከሀምሳ የሚበልጡ ፍልሰተኞች አስከሬኖች መገኘታቸው ይታወሳል።