ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ወረራዋ 10 ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል

Your browser doesn’t support HTML5

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችው ወረራዋ አራተኛ ሣምንቱን በያዘበት በዩክሬን ከተሞች ላይ የምታደርገውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው በአሁኑ ወቅት በሃገር ውስጥ እና ወደ ውጭ ሃገራት የሄዱትን ጨምሮ 10 ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዩክሬኑ ቀውስ ዙሪያ ከአጋሮቻቸው ጋር ተገናኝተው ለመመካከር በያዝነው ሳምንት ወደ አውሮፓ ያመራሉ።