ቻይና ለሩሲያ የመሣሪያ ድጋፍ ለማድረግ አስባለች - ብሊንከን

Your browser doesn’t support HTML5

“ሩሲያ በዮክሬን ላይ እያደረገችው ላለው ጦርነት የሚውል የጦር መሣሪያ ድጋፍ ለማድረግ ቻይና እያሰበች ነው” ሲሉ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ብሊንከን ይህን ያሉት በቱርክ የተከሰተው ርዕደ መሬት ያደረሰውን ጉዳት ለማየት ቱርክ ከማረፋቸው በፊት ነው፡፡

አሜሪካ የቻይና መሆናቸው የተጠረጠሩና የስለላ ናቸው የተባሉ ፊኛዎችን ከሰማይ መትታ ከጣለች በኋላ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ውጥረቱ ተባብሷል፡፡