ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሀሪስ ወደ አፍሪካ ይጓዛሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሀሪስ፣ በቀጣዩ ሳምንት በጋና፣ ታንዛኒያ እና ዛምቢያ ጉብኝት ያደርጋሉ። ምክትል ፕሬዚዳንቷ፣ የፊታችን እሑድ ወደ ጋና የሚገቡ ሲኾን፣ አፍሪካን በመጎብኘት ከፍተኛዋ የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣን ይኾናሉ።

በጉብኝታቸው፥ ዩናይትድ ስቴትስ ከአገሮቹ ጋራ ያላትን አጋርነት፣ ጸጥታንና የኢኮኖሚ ብልጽግናን በማጠናከር ዙሪያ እንደሚመክሩ ከጽሕፈት ቤታቸው የወጣው መግለጫ ያመለክታል።

የመጀመሪያዪቱ እንስት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የኾኑት ካማላ ሀሪስ፣ እንደ መጀመሪያ ጥቁር ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ከአፍሪካ ጋራ ባላቸው የተወላጅነት ግንኙነት፣ አህጉሪቱን መጎብኘታቸው በራሱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው እንደ ኾነ ተንታኞች ይናገራሉ።