የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት፣ መከላከል እና ህክምና

Your browser doesn’t support HTML5

በሴቶች ላይ ስለሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች በሙሉ የጡት ካንሰር ከፍተኛ ትኩረት ያለው ቢሆንም የተለያዩ ጥናቶች ግን በየሁለት ደቂቃው ልዩነት አንዲት ሴት በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ሕይወቷ እንደሚያልፍ ያሳያሉ። በተለይም ኢትዮጵያን ጨምሮ እጅግ ብዙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሃገራት፤ ውስጥ የሚኖሩ ሴቶች፤ ይበልጡን ለመሃጸን በር ጫፍ ካንሰር ተጋላጭ መሆናቸውን የአለም የጤና ድርጅት፤ አለም አቀፍ የካንሰር ቁጥጥር ህብረት አስታውቋል። ህብረቱ አክሎም ይህን የካንሰር ዓይነት ‘በጸጥታ ገዳይ’ ሲል አስቀምጦታል።

ያለ ጊዜው በወር አበባ መሃከል የሚከሰት የደም መፍሰስ፣ ከማረጥ በኋላ የሚከሰት የደም ፍሰት፣ ብሽሽት አካባቢ የሚሰማ ህመም እና አንዳንዴም ደም የተቀላቀለበት ሽንት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምልክቶች እንደሆኑ የጤና ባለሞያዎች ይጠቁማሉ። በአብዛኛውም ይሄ ካንሰር ሁማን ፓፒሎማ ካንሰር ኤች ፒ ቪ ተብሎ የሚጠራው በሽታን ተከትሎ የሚመጣ እንደሆነ ባለሞያዎቹ ይናገራሉ። የኤች ፒ ቪ ክትባትን አስቀድሞ መውስድ ይሄን የካንሰር ዓይነት ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ያግኙ/