የኢትዮጵያው ስድስተኛ ፓትርያርክ ከቪኦኤ ጋር ልዩ ውይይት አደረጉ።
Your browser doesn’t support HTML5
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው በቅርቡ መመረጣቸው ይታወቃል።
ሊቀ-ጳጳስ አባ ማትያስ ባለፈው የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ነበር “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ፓትርያርክ ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ-ጳጳስ ዘአኲስም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ-ተክለ-ኃይማኖት ተብለው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ሊቃነ-ጳጳሳት «ይደልዎ-ይገባዎታል» ብለው በ6ኛ ፓትርያርክነት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲመተ-ፕትርክናቸውን ያከናወኑላቸው።
ፓትርያርክ አባ ማትያስ ማናቸው?
ከልጅነት እስከ እውቀት፣ ከዲቁና እስከ ቅስና፣ ከጵጵስና እስከ ፕትርክና ያለፉበትን ሕይወት ያስቃኙናል።
አዲሱ አበበ ነው ያወያያቸው።