የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ ዕዝ የአህጉሪቱ ደኅንነት ሥጋት አይሎበታል አለ
Your browser doesn’t support HTML5
በመላ አፍሪካ የፀጥታ ሥጋት እየበረታ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄነራል ስቴፈን ታውሰንድ አስታውቀዋል።
ለዕዙ ከተሾሙ ከሦስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ካሜራ ፊት ቀርበው ቃለ ምልልስ ያደረጉት ጄነራል ታውሰንድ ከአሜሪካ ድምፅ የፔንታገን ዘጋቢ ካርላ ባብ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “አህጉሪቱ ውስጥ በታጣቂ ፅንፈኛ ቡድኖች፣ በሩሲያዊያን ቅጥረኛ ተዋጊዎች፣ በኢራን ሥጋት እና በቻይና ወታደራዊ ግንባታዎች የተነሳ ውጥረት አይሏል” ብለዋል።