ከተማሪዎች ዐይን የራቁት የዩኒቨርስቲ መማክርት  

Your browser doesn’t support HTML5

ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲገቡ የዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን እገዛ ማድረግ ከሚገባቸው አካላት መካከል የዩንቨርስቲ ማማክርት ተጠቃሽ ናቸው። ሆኖም ተማሪዎች የዩንቨርስቲ መምክርትን የሚያገኟቸው የዓመታት ትምህርታቸውን አጠናቀው መልቀቂያ ለማግኝት ፊርማ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ነው።

ለመሆኑ የዩኒቨርስቲ መማክርት በምን መልኩ ለተማሪዎች እገዛ ማድረግ ይችላሉ? ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያ ለመስጠት ሁለት የዲላ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድረጋዋል።

የተማሪዎች መማክርት በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎችን ቢያሳትፉ፣ ተማሪዎች በሚያደርጓቸው የግቢ መሰናዶዎች ላይ ቢገኙና ቢሳተፉ፣ እንዲሁም ደግሞ የተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ተማሪዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ቢረዱ መልካም መሆኑን በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

/ሙሉው ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/