በአኹኑ ወቅት በኢትዮጵያ ለሥራ ፈጣሪዎች ምን ያህል ምቹ ኹኔታዎች አሉ? በሚለው ጉዳይ ላይ ከሳሚያ አብዱል ቃድር ጋራ አጭር ቆይታ አድርገናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በኢትዮጵያ ለሥራ ፈጣሪዎች ምን ምቹ ኹኔታ አለ?
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ከሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች መካከል፦ የገንዘብ፣ የዕውቀት እና የትስስር ውስንነት እንዲሁም የሥራ ቦታ ችግር ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚኽን ችግሮች የተመለከተችው ወጣቷ ሳሚያ አብዱል ቃድር፣ "የኢትዮጵያ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ማኅበር"ን ከአምስት ዓመት በፊት መሥርታለች፡፡ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ከ400 በላይ አባላትን ያፈራው ማኅበሩ፣ ዘርፈ ብዙ የግንዛቤ ማስጨበጫና የፖሊሲ ቅስቀሳ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡